የሀገር ውስጥ ዜና

በህወሓት ኃይሎች በቆቦ ከተማና በዙሪያው በሚገኙ ሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቀት በአጅጉ አሳስቦኛል – የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

By Tibebu Kebede

September 19, 2021

 

በህወሓት ኃይሎች በቆቦ ከተማና በዙሪያው በሚገኙ ሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በአጅጉ አሳስቦኛል – የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ኃይሎች በቆቦ ከተማና በዙሪያው ባሉ የገጠር ከተሞች ሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈጸሙ መሆናቸው በእጅጉ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በህወሓት ወረራ ስር ባሉት አካባቢዎች በሚኖሩ ሲቪል ሰዎች ላይ የቤት ለቤት አደጋና ግድያ፣ ዝርፊያ እንዲሁም በመሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እተየፈጸመ መሆኑን ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ የሚያደርገውን ምርመራ እንደሚቀጥልና በግጭቱ የሚሳተፉ ወገኖች በማናቸውም ወቅት ሲቪል ሰዎችን የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲያከብሩም አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!