የሀገር ውስጥ ዜና

መከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ የደሴ ከተማ ወጣቶች አሸኛኘት ተደረገ

By Meseret Awoke

September 20, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሃገር መከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ የደሴ ከተማ ወጣቶች አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

ወጣቶቹ “ለእናት ሃገራችን በችግሯ ጊዜ ቀድመን መስዋእት ልንሆንላት መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ወስነናል” ብለዋል።

“መከላከያን ለመቀላቀል የወሰነው በራሳችን ፈቃድ ነው፣ የኢትዮጵያን ጠላቶች ለመመከትና ሃገራችን ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ ተዘጋጅተናል” ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አበበ ገ/መስቀል÷ ወጣቶች በራሳቸው ፈቃድ የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ያሳዩት ተነሳሽነት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በደሴ ከተማ በተሰራው ስራ ጥሩ ውጤት መገኘቱን ገልጸው÷ ሌሎች ወጣቶችም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ለሀገር ደጀን እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!