የሀገር ውስጥ ዜና

የውጪ ተጽዕኖን ለመቋቋም ሕዝቡ አንድነቱን ማጠናከር እንዳለበት ተገለጸ

By Meseret Awoke

September 20, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሸባሪው ህወሓት ጋር በመሆን በሀገር ላይ ተጽአዕኖ ለማሳደር የሚሞክሩ የውጭ ኃይሎችን ለመቋቋም ሕዝቡ አንድነቱን ማጠናከር እንዳለበት አቶ ገላሳ ዲልቡ ገለጹ።

የቀድሞ የኦነግ ሊቀመንበር ገላሳ ዲልቡ ÷ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር በመሆን በሃገር ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚሞክሩ የውጭ ኃይሎችን ለመቋቋም ሕዝቡ አንድነቱን ማጠናከር ይኖርበታል ብለዋል።

አሻባሪው ትህነግ በ27 ዓመታት ውስጥ በፈፀመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደሎች ተመጣጣኝ እርምጃ ሳይወሰድ የተሰጠውን ትዕግስት እንደፍራቻ በመቁጠር ሕዝብን አጋጭቶ ለውጡን በማደናቀፍ እና በሕዝብ የተነጠቀውን ስልጣን ለመመለስ እየተፍጨረጨረ መሆኑን አቶ ገላሳ ተናግረዋል።

ይህንኑ ዓላማውን ለማሳካትም የውጭ ኃይሎችን መከታ አድርጎ የኢትዮጵያ ህዝብን በመውጋት ላይ ይገኛልም ብለዋል።

እንደ አቶ ገላሳ ÷ አሸባሪው ቡድን ከውጭ ግብር አበሮቹ ጋር በመሆን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

የሰው ሕይወት እንዲጠፋ፣ ንብረት እንዲወድም በማድረግ ሕዝብን በማጋጨት ሠላምና መረጋጋት በሃገር ውስጥ እንዳይሰፍን ብዙ ሰርቷልም ነው ያሉት።

አሸባሪው ትህነግ በፈፀማቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያ በደሎች ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ የለውጥ ኃይሉ ያሳየውን ትዕግስት እንደፍራቻ በመቁጠር በዚህ ሃገር ተድርጎ የማይታወቅ የሽብር ስራዎችን እየፈጸመ ይገኛል ማለታቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!