የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ  እርዳታ ለማድረስ ብሪታኒያ ከመንግስት ጎን ነች-የብሪታኒያ ልዩ መልዕክተኛ

By ዮሐንስ ደርበው

September 20, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ እና ያስሚን ዎሃብረቢ ከብሪታኒያ ልዩ መልዕክተኛ ኒክ ዳየር ጋር በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ረሃብን ለመከላከል በሚሰሩ ስራዎች እና የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የቆየ መሆኑን በመጥቀስ ብሪታኒያ በኢትዮጵያ አፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ መንግስትን እንደምትደግፍ መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡