በሱዳን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሄደ ተባለ
በተለያዩ ሚዲያዎች አሁን እንደተዘገበው ማንነታቸው ያልተገለጸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉ አካላት በካርቱም ኦምዱርማን የሚገኙትን የሀገሪቷን የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለመቆጣጠር ሙከራ ማድረጋቸውም ነው የተገለፀው፡፡ መንግስት ሁኔታውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
በአሁኑ ሠዓት ታንኮች ወደ ኦምዱርማን ድልድይ እና ወደ ሀገሪቷ ፓርላማ ህንፃ ተጠግተው መንገዱን በመዘጋት እንደተቆጣጠሩት ሲገለፅ በአካባቢው የጸጥታ አካላት እንደተሰማሩም ነው የተመላከተው፡፡
በካርቱም የሱዳን የጸጥታ አካላት ናይልን ከ ኦምዱርማን የሚያገናኘውን ድልድይ ቢዘጉም፣ በአካባቢው ሁኔታዎች ተረጋግተው እንቅስቃሴዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ መቀጠላቸው ነው የተሰማው፡፡
አንድ የመንግስት ቃል አቀባይ በሀገሪቷ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ የተቀነባበረውን ሴራ የመሩ አካላት ሲቪሎችና ወታደራዊ ኃይሎች መያዛቸውን ገልጿል፡፡
በመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የኦማር አልበሽር የቀድሞ አገዛዝ ቅሪቶች እንደተሳተፉ የተጠቀሰ ሲሆን ከ 40 በላይ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
አልጀዚራ ያነጋገራቸው ወታደራዊ ምንጮች አንደገለፁት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሊደረግ እንደሚችል ቀድሞ መረጃ ነበረን፤ ለዛም ነው ሁኔታውን ለመቀልበስ የቀለለን
ብለዋል፡፡ እስካሁን ድረስ የሀገሪቷ መንግስት በጉዳዩ ላይ መግለጫ አልሰጠም፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ እና ቲ አር ቲ
