የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ሴክተር አመታዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

September 21, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሴክተር ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

በጉባኤው የ2013 በጀት አመት አፈጻጸም ግምገማና የዕውቅናና ማበረታቻ ስነ ስርዓት ፣የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ ካርታ የቀጣይ 10 አመታት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡