የሀገር ውስጥ ዜና

ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጎብኙ

By Feven Bishaw

September 21, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምድር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ሃላፊዎች እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተከናወነ ያለውን እረፍት አልባ የሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም ያደነቁ ሲሆን ምስጋናም አቅርበዋል።