ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ ሕብረት የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል ያለመ ዘመቻ ይፋ አደረገ

By Meseret Demissu

September 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት “ለጥላቻ ንግግር ቦታ የለም” በሚል መሪ ቃል የጥላቻ ንግግርን ለመካላከል ያለመ ዘመቻ ይፋ አድርጓል።

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ከምሥራቅ አፍሪካ የተመድ ሰብአዊ ድርጅት ጋር በመሆን የአለም የሰላም ቀንን በታንዛንያ አክብሯል።

በዚህ ወቅት ሕብረቱ በወጣት የሰላም አምባሳደሮች የሚመራ “ለጥላቻ ንግግር ቦታ የለም” የሚል ዘመቻ ይፋ አድርጓል።

ዘመቻው በማኅበራዊ ሚዲያ የትሰስር ገጾች ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ግለሰቦች የሚመራ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ከጥላቻ ነጻ የሆነ ውይይትን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም የጥላቻ ንግግር አስከፊነትንና የሚያመጣውን መዘዝ በተመለከተ ዘመቻው ትምህርት እንደሚሰጥ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!