የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ከንቲባዋ የአዲስ አበባን ወጣቶች አመሰገኑ

By Feven Bishaw

September 21, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ወጣቶች ለከተማችሁ ብሎም ለኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነት እያበረከታችሁ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ሲሉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ገለጹ ።

አክለውም “እኔ የከተማዬ የሰላም ዘብ ነኝ” በሚል መርህ መሰረታዊ የሰላምና የፀጥታ ስልጠና የወሰዱ 27 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በክፍለ ከተሞች ወደ ስራ በመግባት ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።