Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ለሲ አይ ኤ ሲሰልል ነበር ባለችው ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ጥር 27፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ለአሜሪካው የስለላ ድርጅት (ሲ አይ ኤ) መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ ነበር ባለችው ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈች።

የኢራን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሚር ራሂምፖው የተባለው ተከሳሽ የሀገሪቱን የኒውክሌር ፕሮግራም የሚመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችን ለአሜሪካ አሳልፎ ሲሰጥ እንደነበር መረጋገጡን አስታውቋል።

ለዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከአሜሪካ መቀበሉን ነው የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ የገለጹት።

በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ አሚር ራሂምፖው በተባለው ተከሳሽ ላይ የሞት ፍርድ ቅጣት ማስተላለፉ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈም ሁለት አሜሪካውያን ሰላዮች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የ10 ዓመትና 5 ዓመት እስር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

ስማቸው ያልተጠቀሱት እነዚህ ግለሰቦች በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሲ አይ ኤ ውሳኔውን አስመልክተው እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም።

በኢራን እና በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የነበሩት ጀኔራል ቃሲም ሱለይማኒ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ መገደላቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን እና ቴህራን ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

 

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.