Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ኮቪድ 19 በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በድሬዳዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኮቪድ 19 ስርጭት አሳሳቢ በሆነ መልኩ እየተሰራጨ መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አሰወታወቀ።

በዴልታ ዝርያ ምክንያት የተከሰተውን ሶስተኛው የኮቪድ 19 ማዕበል የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን ለማሳተፍ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ እንዳሉት÷ በየቀኑ በአስተዳደሩ ከሚመረመሩት ውስጥ 20 በመቶ ቫይረሱ እየተገኘባቸው እንደሆነና ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአምስት ሠዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።

የቫይረሱ ሦስተኛው የስርጭት ማዕበል የተከሰተና የቫይረሱ ባህሪም ተለዋዋጭ በመሆኑ፣ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሠዎች ቁጥር እየጨመረ ስለሚገኝም የስርጭት መጠኑን ለመግታት የተቀናጀ አሰራርን መተግበር እንደሚያስፈልግ ነው ሃላፊዋ የገለፁት።

የኮቪድ 19 የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው መንገድ ባለመተግበራቸውና በሚስተዋለው መዘናጋት ሳቢያ በሽታው በፍጥነት እንዲስፋፋ መሆኑን የድሬዳዋ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ህዝቅያስ ታፈሰ ገልጸዋል።

በዚህም የጥንቃቄ እርምጃዎችን መተግበርና የመከላከያ ክትባትን መከተብ አማራጭ የለውም ብለዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ በድሬዳዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሠዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለአብነት ያህል ከአዲሱ ዓመት በኃላ ደግሞ 285 ሰዎች ሲያዙ አምስቱ ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በድሬዳዋ 229 ሻይረሱ ያለባቸው መሆኑና 16ቱ በህክምና ተቋም በማገገም ላይ ሲሆኑ÷ አምስቱ በፅኑ ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የኮቪድ 19 በድሬዳዋ መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ 5ሺህ 818 በበሽታው ሲያዙ እስከ ትናንት ድረስ የ91 ሠዎች ህይወት ስለማለፉ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.