Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 22 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ከ413 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል ከ413 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 22 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው።

በመጀመሪያው ዙር ግንባታቸው የተጠናቀቁ 8 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የአርሶ አደሩን የልማት ተጠቃሚነት እያሳደጉ መሆኑን የክልሉ አነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ምራ መሐመድ ተናግረዋል።

የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶቹ 2 ሺህ 600 ሄክታር መሬት ያለማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ፕሮጀክቶቹ ከ3 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።

አርሶ አደሮች በ2 ሄክታር መሬት በመስኖ ልማት ስራ የተሻለ ገቢ ለማግኘት ማቀዳቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በየአካባቢው ዘመናዊ የመስኖ ተቋማት አለመኖራቸውን የተናገሩት አርሶ አደሮች፥ ያለ ምንም ጥቅም ሲፈሱ የነበሩ ወንዞችን በመስኖ በመጥለፍ ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረጉ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.