Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለህልውና ዘመቻው 45 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሕልውና ዘመቻው 45 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቢያዝን እንኳሆነ÷ ድጋፉ ከሠራተኛው የወር ደመወዝ፣ በድርጅቱ ውስጥ ካሉ ሲቪክ አደረጃጀቶች፣ ከሠራተኛው መረዳጃ ማኅበር እና ከሠራተኛ ገንዘብ እና ቁጠባ ማኅበር የተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል።

ሥራ አስፈፃሚው ከ4 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ችግር ላይ መሆኑን ገልጸዉ÷ ሁሉም ሰው የሚችለውን ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ድጋፉ በሽብርተኛው ትህነግ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እና አሸባሪዉን ወራሪ ቡድን በግንባር እየተፋለመ ላለው የፀጥታ ኀይል የሚዉል ነዉ ተብሏል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው እንደ ተቋም ከ17 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ጥሩ ብርሃን ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን በመገንባት የስልጠና ተግባሩን እንዲጀምር እና የመጀመሪያ ዙር ስልጣኞችን እንዲያስመርቅ እገዛ አድርጓል ብለዋል።

ከ75 በላይ የድርጅቱ የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም ከ34 በላይ የሚሆኑ የድርጅቱ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችና ማሽኖች ወደ ግንባር ተሰማርተው የሚፈለገውን ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

ሠራተኞችም ለሕልውና ዘመቻው ገንዘብ መስጠት ብቻ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከ80 በላይ ሠራተኞች የተጠባባቂ ኃይል ስልጠና ወስደው መመረቃቸዉንና ደም መለገሳቸዉን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.