Fana: At a Speed of Life!

በብርሸለቆ ለሠራዊት አባላት የማዕረግ ሹመት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሠራዊት አባላት የማዕረግ ሹመት ተሰጠ፡፡

የማዕረግ እድገት የተሰጠው የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑና በመልካም የስራ ውጤት የላቀ አፈፃፀም ያመጡ የባለ ሌላ ማዕረግተኞች፣ ለመስመራዊ መኮንኖች እና ለከፍተኛ መኮንን የሠራዊት አባላት ነው፡፡

የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከፍተኛ የሠራዊት አመራሮች እና አባላት እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን ወረዳ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል ፡፡

ለተሿሚዎች ማዕረግ በማልበስ ንግግር ያደረጉት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮ/ል ጌታቸው አሊ÷ ሰራዊታችን ከሀዲ ጠላትን በመፋለም ድል እያስመዘገበ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተሰጣችሁን ግዳጅ በስኬት በመወጣት ለማዕረግ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡

የማዕረግ ዕድገት ያገኙ የሠራዊት አባላት በበኩላቸው÷ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ተልዕኮ በላቀ ውጤት ለመፈፀም ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው አንስተዋል፡፡

አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እና አሽከሩ ሸኔን በመደምሰስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በጀግንነት ለማስከበር መዘጋጀታቸውን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.