Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የከተሞችን አገልግሎት ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ሶፍትዌሮችን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተሞችን አገልግሎት ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ ያስችላሉ ያላቸውን ሶፍትዌሮች አስተዋወቀ።

በሁሉም ከተሞች አገልግሎትን ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ ታስበው የተዘጋጁት ሶፍትዌሮቹ÷ ኢንጂነር አይሻ መሀመድና ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም የክልል ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው የተተዋወቁት፡፡

ዜጎች በመልካም አስተዳደር ችግሮችና ፍትሀዊ አገልግሎት ባለማግኘት በተደጋጋሚ የሚያነሷቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ 4 ሶፍትዌሮች ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር የክልል ከተሞች ስራ ላይ እንዲያውሏቸው በይፋ አስጀምሯል፡፡

ሶፍትዌሮቹም÷ የከተሞች ዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ሶፍትዌር፣ የኮንስትራክሽን እሴት መመዝገቢያ ሶፍትዌር፣ የከተማ ቤቶች መረጃ መመዝገቢያ ሶፍትዌር እና ወረቀት አልባና የቢሮ መረጃ ልውውጥ አገልግሎት አሠራር ናቸው ተብሏል፡፡

ሶፍትዌሮቹ ሥራ ላይ በትክክል ከዋሉ የከተሞችን አገልግሎት አሰጣጥ ያዘምናሉ ተብሎ እንደታመነባቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.