Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮቪድ 19 በአንድ ቀን ብቻ የ43 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ የተከሰተው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር አሰታወቀ፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በወቅታዊ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በጠና የታመሙ ሰዎች ቁጥር 800 መድረሱን የገለፁት ሚኒስትሯ÷ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወረርሽኙ ብዙ ጉዳት ሊያደርስ እደሚችል ነው የጠቆሙት፡፡
በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ የሚገኘው ወረርሽኙ÷ የሚያሳድረውን ጉዳት ለመቀነስም አንዱ ቁልፍ መከላከያ ዘዴ ክትባት ነው ብለዋል፡፡
በዚህም ቀድሞ የነበረው መመሪያ መሻሻሉን የገለፁት ሚኒስትሯ÷ አሁን እድሜአቸው 18 እና ከ18 አመት በላይ ለሆኑ ሁሉ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች ጭምር ክትባት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በዓላትን ጨምሮ ሌሎች በቀጣይ ያሉ አሳሳቢ ሁኔታዎችን በተመለከተም ስርጭቱ ን የሚያባብሱ ሁኔታዎችን በመቀነስ ረገድ ሁሉም ሰው በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአዲሱ ሙሉነህ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version