የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ደሚቱ ከምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

September 22, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኩ ዶንግዩ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለው አጋርነትና ትብብር በተለይም ባለፉት ዓመታት አንበጣን በመከላከል፣ በልማት እና በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አያይዘውም አምባሳደር ደሚቱ÷ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የምግብ ሜካናይዜሽን፣ በማዳበሪያ አቅርቦትና የአግሮ ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን በማጠናከር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት አብራርተውላቸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩም ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ለአምባሳደሯ እንዳረጋገጡላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!