Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ከ27 ሺህ 500 በላይ በጎ ፍቃደኞች ወደ ስራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ተውጣተው በፈቃደኝነት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ከ27 ሺህ 500 በላይ ወጣቶች ከዛሬ ጀምረው ወደ ስራ ስምሪት ገብተዋል።

ወጣቶቹ በከተማዋ ላይ ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር በራሳቸው ተነሳሽነት አካባቢያቸውን ለመጠበቅ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ናቸው።

“እኔ ለከተማየ ሰላም ዘብ ነን ” የሚል መሪ ቃል ያነገቡት ወጣቶቹ የከተማዋን ሰላም የተረጋገጠ ለማድረግ የስራ ስምሪቱን በወሰዱበት መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በምክትል ከንቲባ ማእረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማእከል ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ሌሎች የከተማ አስተዳድሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

‘’የከተማ አስተዳድሩ የዴሞ ክራሲ ግንባታ ማዕከል ሃላፊ ለከተማችሁ ሰላም አለኝታ ለመሆን ፈቃደኛ ሆናችሁ የህዝባችሁን ሰላም እንዲሁም ደህንነቱን ለማረጋገጥ ስልጠና የወሰዳችሁ ተመራቂዎች ላሳያችሁት ቁርጠኝነት ምስጋና ይገባችኋል’’ ብለዋል።

ጠላት ሃገርን ሰላሟን ለማናጋት በሚሯሯጥበት በዚህ ወቅት የከተማዋ ህዝብ የጸጥታ አካላትን ለመደገፍ ያሳየው ድጋፍ የሚደንቅ ነውም ብለዋል።

ዛሬ መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና ወስዳችሁ ከጸጥታ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር ሆናችሁ የጥፋት ቅጥረኞችን እና ጸረሰላሞችን ለመዋጋት ደጀን ለመሆን በመነሳታችሁ እና የተሰለፋችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ኮርተንባችኋልም ነው ያሉት።

አሁን ያጋጠመንን ችግር ቀዳሚ ሆነን ለመከላከል እና ከፊታችን ላለው የኢትዮጵያ የመበልጸግ ተስፋ ለመድረስ አቅምና ሰራዊት ናችሁና የተሰጣችሁን ሃላፊነት በብቃት እንደምትወጡም ባለ ሙሉ ተስፋ ነን ሲሉም ተናግረዋል።

በዚህም ለቀጣዩ ትውልድ አሻራችሁን እንደምታስቀምጡ እርግጠኞች ነን ብለዋል አቶ መለስ አለሙ።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.