Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ምክር ቤት የዜጎች ፍላጎት የሚንፀባረቅበት እንደሚሆን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ በሚመሰረተው ምክር ቤት የሚወጡ ሕጎች፣ ደንቦች እና ውሳኔዎች የህዝቦችን እኩልነት የሚያረጋግጡና የሕዝቦች ፍላጎት የሚንፀባረቅበት ምክር ቤት እንደሚሆን አዲስ ተመርጠው የመጡ የምክር ቤት አባላት ገለፁ።

ለአዲስ የምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ የአሰራር እና የአባላት ሥና-ምግበር ደንብ ዙሪያ እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ወቅት አባላቱ እንደገለጹት÷ የዜጎችን ዘላቂ ሰላም፣ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲያዊ፣ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችና ነፃነቶችን ለማረጋገጥ የሚተጋ ምክር ቤት እንደሚሆን ከዳውሮ ዞን ተወክለው የመጡት አቶ ተስፋዬ በምለኪ ገልፀዋል።

በተመሳሳይም ከሲዳማ ክልል ተመርጠው የመጡት ወይዘሮ አለሚቱ አበበ የዘንድሮው ምክር ቤት ከባለፈው ምክር ቤት የተለየና በተሻለ መልኩ አስፈጻሚ አካላትን በመቆጣጠር፣ የወጡትን ህጎች ተከታትሎ ተፈጸሚነታቸውን የሚያረጋግጥ ምክር ቤት ይሆናል ብለዋል፡፡

አዲሱ ምክር ቤት የሴቶች ተሳትፎ የሚጨምርበት እና የተገራ አስተሳሰብ ይዘን ህዝባችንን ወደ ብልጽግና የምናሻግርበት ይሆናል ሲሉም መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.