በጋምቤላ ክልል የሀገር ህልውናን ለማስከበር ግንባር ለዘመቱ የልዩ ሀይል ቤተሰብ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሀገር ህልውናን ለማስከበር ግንባር ለዘመቱ የልዩ ሀይል ቤተሰብ 10 ሺህ የሚጠጋ ደብተር እና የመማሪያ ቁሳቁስ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ድጋፍ አደረገ፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት ÷ድጋፉ የሀገር ህልውናን ለማስከበር ግንባር ላይ ለሚገኙ የልዩ ሀይል ቤተሰብ ተማሪዎች የሚውል ነው ብለዋል ፡፡
ለልዩ ሀይል ቤተሰብ ለ1 ሺህ 200 ተማሪዎች የሚሆን 10 ሺህ የሚጠጋ ደብተር እና እስክርቢቶ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
ልዩ ሀይሎቹ ሀገርን ለማዳን እያደረጉ ላለው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸው፥ በቀጣይም ሌሎች ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ልዩ ሀይል አዛዥ ኢንስፔክተር ኮንግ ሪክ በበኩላቸው÷ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ ሌሎች ተቋማትም የልዩ ሀይሉን ቤተሰብ በመደገፍ ረገድ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል፡፡
የልዩ ሀይል ቤተሰብ ተማሪዎች ቤተሰቦች የሀገራቸውን ህልውና ለመከላከል ወደ ግንባር ቢዘምቱም በመማሪያ ቁሳቁስ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳያቋርጡ ድጋፍ መደረጉ እንዳስደሰታቸው አስረድተዋል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሯች ባየክን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ሲል ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!