Fana: At a Speed of Life!

የከተሞች ተቋማዊ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በ859 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እየተተገበረ እንደሚገኝ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተሞች ተቋማዊ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በ859 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በ117 ከተሞች እየተተገበረ እንደሚገኝ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ወደ ሶስተኛ ምእራፍ የተሸጋገረውን የከተሞች ተቋማዊ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ሶስተኛ ዙር ላይ የሚገኘው ፕሮግራሙ በ2001 ዓ.ም በ19 ከተሞች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መተግበር የጀመረ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ደግሞ የተያዘለትን በጀት በማሳደግ በ44 ከተማዎች ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ማሻሻያ፣ ፈንድ ሞቢላይዜሽንና ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አምላኩ አዳሙ 3ኛው ዙር የከተሞች መሰረተ-ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በ859 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ፕሮግራሙ በከተሞች ከፍተኛ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር፣ የተለያዩ የመሰረተ ልማቶች እና የአሰራር ሥርዓቶች እንዲዘረጉ እና በአጠቃላይ የከተሞች የማስፈጸም አቅም እያደገ እንዲመጣ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ማለታቸውን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሮግራሙ ተግባራዊ በሆነባቸው 11 ዓመታት ውስጥም ከ800 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለም ተጠቁሟል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.