የሌሶቶ ቀዳማዊት እመቤት የባለቤታቸውን የቀድሞ ሚስት በመግደል ክስ ተመሰረተባቸው
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሌሶቶ ቀዳማዊት እመቤት ማይሲያህ ታባኔ የባለቤታቸውን የቀድሞ ሚስት በመግደል ክስ ተመሰረተባቸው።
ሊፖሌሎ ታባኔ የቀድሞ ባለቤታቸው ቶማስ ታባኔ በፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2017 ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ ከመፈፃማቸው ሁለት ቀናት አስቀድሞ ከቤታቸው ውጭ መገደላቸው ተነግሯል።
የ42 ዓመቷ ቀዳማዊት ማይሲያህ ታሃባኔ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ግድያ ክስ መመስረቱን ተከትሎ በማቆያ ክፍል እንዲቆዩ ተደርገዋል።
ከዚህ ባለፈ ቀዳማዊት እመቤቷ ከቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ጋር የነበሩትን ግለሰብ ለመግደል በመሞከር ክስ እንደተመሰረተባቸው ነው የተነገረው።
የቀድሞዋ ቀዳማዊ እመቤት ግድያ በወቅቱ በትንሷ ንጉሳዊ ሀገር እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩን ሲ ኤን ኤን በዘገባው አስታውሷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ በፓለቲካዊ ግፊት የፓርቲያቸውን ውሳኔ እንደሚያከብሩ እና ስልጣን እንደሚለቁ ባለፈው ወር መግለፃቸው ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ የቀዳማዊት እመቤቷ ጠበቃዎች አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥሪት ስኬታማ እንዳልሆነ በዘገባው ተመላክቷል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision