Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል የመስቀል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤መስከረም 16፤ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የሀረሪ ክልል የመስቀል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ክልሉ በመልዕክቱ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ለክልል የፀጥታ አባላትን እንኳን ለ2014 ዓ.ም የመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ብሏል፡፡

ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ራሱን በመጠበቅ እና የመካላከያ መንገዶችን በአግባቡ በመተግበር እንዲሆንም የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተለይም በክልሉ መስከረም 20 የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ እንዲሆን መላው የክልሉ ነዋሪ ድጋፉንና ተሳትፎውን እንዲያጎለብት ጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.