የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ነው

By Meseret Awoke

September 27, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የመስቀል በዓል በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው።

በበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ህሩያን እስጢፋኖስ ጥፍጤን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

ሥራ አስኪያጁ ለምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን÷ ምዕመናን በዓሉን በሽብር ቡድኑ ህወሓት ወረራ የተፈናቀሉ ዜጎችን በማሰብ እና በመርዳት እንዲያከብሩም አሳስበዋል።

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ጎንደር ዞን ሰባት የሚደርሱ አብያተ ክርስቲያናትን ማውደሙን ም አንስተዋል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!