የሀገር ውስጥ ዜና

በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

September 27, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ትህነግ ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመስቀልን በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

አቶ አበባው ተፈራ የተባሉ የከተማዋ ባለሀብት እና የቢጄአይ ኢትዮጵያ ሠራተኞች ናቸው በሁለት የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ 853 ተፈናቃዮች ማዕድ ያጋሩት።

በኮምቦልቻ ከተማ ከ20 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥ 5 ሺህ የሚሆኑት በመጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡