የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን የተመድ የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ዋና የፈጠራ ስራ ኃላፊ በመሆን ተሾሙ

By Meseret Awoke

September 28, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የኢሴክስ መስራች ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን የተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ) የአፍሪካ ዋና የፈጠራ ስራ ኃላፊ በመሆን ተሾሙ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅትን (ኢ.ሲ.ኤክስ) እንዲሁም ብሉ ሙን የተሰኙ ተቋማትን በመመስረት እና በመምራት የሚታወቁት ዶክተር እሌኒ ለዚህ አዲስ ስራቸው ወደ ኒውዮርክ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ የወጣቶች የፋይናንስ ፈጠራ አብዮት ቲምቡኮትን በማስጀመር ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወቱ ዩኤንዲፒ በድረ ገጹ ማስነበቡን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ ዲጂታላይዜሽንን ማሳደግ እና ወጣቶችን ማበረታታት ትኩረት አደርገው ይሰራሉ ብዩ አምናለሁ ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ረዳት ዋና ጸሐፊ እና የዩ.ኤን.ዲ. ፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁንና ኢዚያኮንዋ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!