ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በአሁን ሰአት የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው 101 አንቀፆች ባሉት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በረቂቅ አዋጁ መሰረት ካለፈው ምክር ቤት 61 የነበሩት አጠቃላይ የአስፈፃሚ አካላት በአዲሱ ምክር ቤት 46 ሆኖ ሲቀርብ፣ የካቢኔ አባላት ደግሞ 24 እና በከንቲባ እንደ አስፈላጊነታቸው የሚሰየሙ ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ አዳዲስ የካቢኔ አባላት የሆኑ ተቋማትን መያዙን ከከተማው ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!