የሀገር ውስጥ ዜና

በኮሮና ቫይረስ በመያዝ የተጠረጠሩ ኢትዮጵያውያን ለሁለተኛ ጊዜ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋገጠ

By Tibebu Kebede

February 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ለሁለተኛ ጊዜ በኖቭል ኮሮና ቫይረስ በመያዝ የተጠረጠሩ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን አስታወቀ።

ባለፈው ሰኞ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ አንድ ቻይናዊና ሶስት ኢትዮጵያውያን በቫይረሱ በመያዝ ተጠርጥረው ክትትል እየተደረገላቸው እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።

ሚኒስቴሩም የግለሰቦችን ናሙና ወደ ደቡብ አፍሪካ በመላክ ተጨማሪ ምርመራ አስደርጓል።

በደቡብ አፍሪካ በተደረገው ምርመራም አራቱም ሰዎች ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም አራት ኢትዮጵያውያን በቫይረሱ ተጠርጥረው በተደረገላቸው ምርመራ ነጻ መሆናቸው መረጋገጡ የሚታወስ ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision