Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ለወንዶች ከሴቶች እኩል የወሊድ ፈቃድ ልትሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፊላንድ ለወንዶች ከሴቶች እኩል የወሊድ ፈቃድ ልትሰጥ መሆኑ ተነገረ።

አሁን ባለው አሰራር በፊንላንድ የወለዱ እናቶች ከአራት ወራት በላይ የወሊድ ፈቃድ ሲያገኙ ወንዶች ደግሞ ሁለት ወር ከሁለት ሳምንት ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።

ውሳኔው አባቶች በተለይም ከልጆቻቸው ጋር ተጨማሪ ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የጾታ እኩልነትንና ደህንነትን ለማበረታታት የታሰበ ሲሆን ክፍያን እንደሚጨምርም ታውቋል።

ይሁን እንጅ በአማካይ ከአራት ወንዶች አንዱ ብቻ የተሰጠውን ፈቃድ እንደሚጠቀምበት ነው የተገለጸው።

አሁን የታቀደው የፈቃድ አይነት ወላጆችን ብቻ የሚመለከት ነው።

የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ባለፈው ወር ሃገራቸው አሁንም የፆታ እኩልነትን በተገቢው መልኩ ለማረጋገጥ መስራት ይገባታል ማለታቸው ይታወሳል።

የፊንላንድ የጤናና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አይኖ ካይሳ ፔኮነን በበኩላቸው፥ የወላጆችን ግንኙነት ለማጠናከር ባለመ መልኩ ቤተሰቦች በሚያገኙት ጥቅማ ጥቅም ላይ መሰረታዊ ለውጥ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ለወላጆች በሚሰጠው የሥራ ፈቃድ ላይ የሚደረገው ለውጥ የፊንላንድ መንግሥትን ተጨማሪ 110 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስወጣው ተገምቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.