“በአዲስ መንፈስ አዲስ ውል – መንግስት ምስረታ እና ሃገር ግንባታ” በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ወግ አንድ ጉዳይ “በአዲስ መንፈስ አዲስ ውል – መንግስት ምስረታ እና ሀገር ግንባታ” በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ውይይቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከጽህፈት ቤቱ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ፍስሐ ይታገሱ እንዳሉት÷ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ማለትም ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት ፣ በመንግስት እና በሕዝቦቹ መካከል መተማመን እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶችን መገንባትን ያካትታል፡፡
ተሳታፊው አክለውም ያለንበትን ጊዜ ልዩ የሚያደርገውም እነዚህ ጉዳዮች ጎንለጎን እየተስተናገዱ መሆናቸው ነው ብለዋል፡፡
በአዲሱ የመንግስት ምስረታ እነዚህ የሀገረ መንግስት ግንባታ ልዩ ገጽታዎች ቁልፍ የትኩረት መስኮች መሆን እንዳለባቸውም አንስተዋል፡፡
ኮለኔል ፍቅረየሱስ ከበደ በበኩላቸው÷ የቀጠናው ተለዋዋጭነት እና ተጋላጭነት ስጋቶች ትንተና እና ግምገማ ላይ በመመስረት የብሔራዊ ደህንነት መዋቅሩ ይሻሻላል ብለዋል።
አሁን ያለው ክልላዊ የፀጥታ ከባቢው የተሟላ እና የማይለዋወጥ መሆኑን አንስተዋል።
ስለሆነም የኢትዮጵያ የደህንነት ዘርፍ አወቃቀር ለእንደዚህ ዓይነቱ ትንታኔ ምላሽ የሚሰጥ እና ገለልተኛ እንዲሁም በሙያዊ ተቋማዊ አደረጃጀት ውስጥ እንዲቆም እንደሚደረግ ኮለኔል ፍቅረየሱስ ገልጸዋል።
ዶክተር ፍፁም አሰፋ÷ በተስፋ እና በፈተናዎች በተሞላው ዘመን ውስጥ እንገኛለን ብዋል፡፡
አክለውም አዲሱ መንግሥት ወቅታዊ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን ይፈትሻል፤ ይፈታል ያሉ ሲሆን÷ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን ፣ በኢኮኖሚው ውስጥ ፍትሃዊ ተሳትፎን ማንቃት ላይ በትኩረት ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
በገበያ መር ኢኮኖሚ ኢትዮጵያ በ 2014 የአፍሪካ የብልፅግና ነፀብራቅ እንድትሆን መንገድ ይጠርጋል ሲሉ ገልጸዋል ዶክተር ፍጹም ፡፡
ይህንን እውን ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የመሪነት ሚና መጫወት እንዳለበትም አንስተዋል፡፡
“የአዲሱ ኮንትራት እና የሚቀጥሉት የአሥር ዓመት ተቋማዊ ግንባታ ፍኖተ ካርታ መሰረት የመንግስት ሥራዎች ሙሉ በሙሉ በሕግ ደንቦች ፣ በመመሪያዎች እና በሙያዊ የመንግሥት ሠራተኞችን በማብቃት ላይ ይሆናል” ያሉት ደግሞ አቶ በዛብህ ገብረየስ ናቸው፡፡
የመንግስት ሰራተኛ የሥነ ምግባር ደንብ በማረጋገጥ ለሕዝብ ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦት ላይ ትኩረት እንደሚደረግም አንስተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!