Fana: At a Speed of Life!

ለኢሬቻ በዓል አከባበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻን በዓል ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ለበዓሉ አከባበር የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
በበዓሉ አከባበር ላይ ምንም አይነት የፖለቲካ ፓርቲ ባንዲራ ይዞ መምጣት የተከለከለ መሆኑንም ገልጿል።
የኢሬቻ በዓል መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም ሆራ አር ሰዲ ይከበራል።
የበዓሉን አከባበር የሚያስተባብረው የቴክኒክ ኮሚቴ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ከበደ ዴሲሳ በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።
በዓሉን ለማክበር የሚመጣው ሕዝብ አባገዳዎች በወሰኑት መሰረት በዓሉን ከሚገልጹ ነገሮች ውጭ ምንም አይነት የፖለቲካ ፓርቲ ባንዲራ መያዝ የተከለከለ መሆኑን ተናግረዋል።
በዓሉ በሠላም እንዲከበር ሕዝቡ የተለመደ ትብብሩን ማድረግ እንደሚጠበቅበት የገለጹት አቶ ከበደ በዓሉን ለማክበር የሚመጣ ሕዝብ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ብለዋል።
ከበዓሉ በፊት የተለያዩ ጥናቶች እንደሚቀርቡና ፎረሞች እንደሚዘጋጁም ጠቁመዋል።
የኢሬቻ በዓል ከኦሮሞ ሕዝብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃልም ብለዋል።
ኢሬቻ ማለት ማምለክ እና ማመስገን ማለት ነው፤ ይሄን ስላደረግህልኝ፣ ከክረምት ወደ ብራ ስላሸጋገርከኝ አመሠግናለሁ እየተባለ ፈጣሪ የሚመሰገንበት በዓል ነው።
በኢሬቻ በዓል ሰዎች እርጥብ ሳር ይዘው ወደ ወንዝ በመሄድ ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ እንዲሁም ይለምናሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.