የሀገር ውስጥ ዜና

ትምህርት ሚኒስቴር ለ2014 ለመማር ማስተማሩ ስራ ዝግጅት ከአጋር ድርጅቶች ድጋፍ አገኘ

By Meseret Awoke

September 29, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ለትምህርት ሚኒስቴር የ2014 መማር ማስተማር ስራ ዝግጅት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የመማሪያ ቁሳቁሶች እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች ለሚኒስቴሩ ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡

ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ቦርሳ የአዲስ አበባ እና የክልል የትምህርት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አስረክበዋል፡፡

ሚኒስትሩ÷ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀው÷ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፍ ያደረጉትም የፓንዳ ፓክ ፕሮጀክት እና የአሊባባ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ናቸው፡፡

የቻይና ፋውንዴሽን ፎር ፖቨርቲ አሊቬሽን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!