Fana: At a Speed of Life!

በዞኑ በነበረው የጸጥታ ችግር በ194 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ ገለጹ፡፡
23ኛው ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ዛሬ በአሶሳ ተጀምሯል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ የተጎዱት በ2013 በመተከል በነበረው ግጭት ሲሆን÷ እነዚህም የመጀመሪያ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተምህርት ቤቶች መሆናቸውን ኃላፊው በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል የፈራረሱ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ 69 ሺህ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደነበሩ አቶ ቢኒያም ጠቅሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ከመገንባት ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ጭምር ተዘጋጅቶ እየተሠራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው÷ የሽብርተኛው ህወሓት ቡድን በተላላኪዎቹ አማካኝነት በክልሉ ያደረሰውን ጥፋት ከማውገዝ ባለፈ ችግሩ እንዳይደገም ትምህርት ቤቶቹን መልሶ ለመገንባት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
አመራሮች፣ መምህራን፣ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ወላጆች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተጠናከረ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.