በሐረር ከተማ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በይፋ ተጀመረ

By Tibebu Kebede

September 30, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ተጀምሯል፡፡

መራጩ ህብረተሰብም በተዘጋጁ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ይወክለኛል ለሚለው ድምጹን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተመለከትንበት የምርጫ ጣቢያዎችም የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱም ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መልኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሐረሪ ክልል በሚገኙ 36 ቀበሌዎች 229 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡

ምንጭ:- ኢዜአ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!