ምርጫው የሚወክሉንን መሪዎች ለመምረጥ ያስችለናል – የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል በሚካሄደው ምርጫ በመሳተፍ የሚወክሏቸዉን መሪዎች እንደሚመርጡ በምርጫዉ የተሳተፉ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ።
ምርጫው ለህዝብ ዕድገትና እኩልነት የሚሰራ መንግሥት ለመመስረት ያስችላል ሲሉ ነው የገለጹት ነዋሪዎቹ፡፡
ምርጫ የአንድ አገር ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ማረጋገጫና በጉጉት የሚጠበቅ ክስተት መሆኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ÷ ምርጫ ለዜጎች ሰላም፣ ልማትና እኩልነት የሚተጉ መሪዎችን ወደ ስልጣን ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የምርጫ ካርድ የወሰደ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ይወክለኛል ያለዉን መሪ እንዲመርጥና ካርዱን እንዳያባክንም መክረዋል።
የምርጫ ካርድን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል የሚወክሏቸዉን መሪዎች እንደሚመርጡ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ምርጫው ነጻና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወሰነው መሠረት መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በሶማሌና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው እየተካሄደ ይገኛል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!