የሀገር ውስጥ ዜና

የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ እየሰጡ ነው

By Meseret Awoke

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዲያ ዞን ሌሞ 01 ምርጫ ክልል የሴች ዱና 02 ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ በመስጠቱ ሂደት በነቂስ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ድምጽ በመስጠቱ ሂደት ደሬቴድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችም ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት እንደቀጠለ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!