የሀገር ውስጥ ዜና

የሀረሪ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባኤ ድምፅ ሰጡ

By Meseret Awoke

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በሀረሪ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አዲስዓለም በዛብህ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

የክልሉ አፈ ጉባኤ በአበኮር ወረዳ ሸኪብ ወጣቶች ማዕከል ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን ሲሰጡ እንደተናገሩት÷ ምርጫው በሁሉም ጣቢያዎች ሠላማዊ ሆኖ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ህዝቡ ያለምንም ተፅዕኖ ድምፁን ለፈለገው ፓርቲ እየሰጠ ነው ብለዋል።

ከምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የህዝብን ድምፅ አክበረው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው የገለፁት ወይዘሮ አዲስዓለም÷ ህዝቡም ምርጫው ያለምንም ችግር እየተካሄደ በመሆኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ይመራኛል የሚለውን በንቃት እንዲመርጥ አሳስበዋል።

በሀረሪ ክልል ለሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ከ135ሺህ በላይ ህዝብ ተመዝግቦ በ÷ 229 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፁን በመስጠት ላይ ይገኛል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!