Fana: At a Speed of Life!

ለስድስት ኩባንያዎች የከፍተኛ ማዕድን ምርት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስት ኩባንያዎች የከፍተኛ ማዕድን ምርት ፈቃድ መሰጠቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያዎች ተፈራርመዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው የማዕድን ፍለጋውን አጠናቀውና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ኩርሙክ ጎልድ ማይን ፣ኢትኖ ማይኒንግ እና ኦሮሚያ ማይኒንግ ኩባንያዎች የወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንዲሁም አሊ ሀሚል ካሐዲም የብሮሚን እና ክሎሪን ምርት ፈቃድ ሲወስድ ÷ኪሪፕቶ ማይኒንግ ኤንድ ኬሚካልስ እና ቡሁሚ ማይኒንግ ኩባንያዎች ደግሞ የእምነበረድ ምርት ፈቃድ መውሰዳቸው ታውቋል፡፡

ኩባንያዎቹ ከ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ÷ ከ1 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የስራ እድል መፍጠሩን ከማዕድና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.