Fana: At a Speed of Life!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቃዮች ከ1ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ባደረሰው ጥፋት ከሰሜን ወሎ አካባቢ ተፈናቅለው በደሴና በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ ክተር ፋሪስ ደሊል እንደገለጹት፥ የተፈጠረው ችግር ከባድና አሰቃቂ ቢሆንም ህዝባዊና ተቋማዊ ትብብርን በመፍጠር ኢትዮጵያዊ አንድነት እንዲያብብ አድርጎታል ብለዋል።
ድጋፋችን ከደረሰው አደጋ አንጻር በቂ ነው ባይባልም የወገን አለኝታነታችንን ማሣያ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፥ በድጋፉ ብርድልብስ፣ አንሶላ እና የሽሮ እህሎች ተካተውበታል ነው ያሉት።
በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዎች የእርስ በርስ ትብብር እንዲኖራቸው እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
የወሎ ዩኒቨርሲቲም ድጋፉን ተረክቦ ለተደረገው ድጋፍም አመስግኗል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.