የሀገር ውስጥ ዜና

የደ/ወሎ ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት መምሪያ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻ ድጋፍ አድርጓል

By Feven Bishaw

October 01, 2021

አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት መምሪያ እሰከ አሁን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

የመምሪያው ሀላፊ አቶ መስፍን መኮነን ለፋና ብሮድካስንቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ ግንባር ድረስ በመዝለቅ ከሚፋለሙ የተቋሙ ሰራተኞች ባሻገር እሰከ አሁን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።