የሀገር ውስጥ ዜና

ሁሉም የኢትዮጵያ በአዓላት የኢትዮጵያውያን ፀጋዎች ናቸው – አቶ ጃንጥራር አባይ

By Tibebu Kebede

October 02, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አንኳን ለኢሬቻ በአል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሁሉም የኢትዮጵያ ባህላዊ በአላት የኢትዮጵያውያን ፀጋዎች ናቸው ያሉት አቶ ጃንጥራር ፀጋዎቻችንን ለሕዝባችን አንድነት ፍቅር ወንድማማችንት መጠቀማችን ይቀጥላል ብለዋል።

ኢሬቻ የንጋት የብርሃን የምስራች ማብሰሪያ በአል ነው ፤መስከረም ለኛ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ነው በአንድ በኩል ዘመን የምንቀይርበት በሌላ በኩል ትልልቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በአላትን በፍቅርና በደስታ የምናከብርበት ወር መሆኑ የተለየ ያድርገዋል።

በድጋሜ መልካም የኢሬቻ በአል ይሁንልን ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!