የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ በሚደረገው የመንግስት ምስረታ ላይ ይገኛሉ
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ዘገባውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሃላፊነት ሲመጡ ፕሬዚዳንት ቡሃሪ የመልካም ምኞት መግለጫ መላካቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ናይጄሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጿል።
በኢትዮጵያ በሚካሄደው የመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም እንግዶች እየገቡ ሲሆን ትናንት አዲስ አበባ የገቡት የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፍሬይ ኦኒዬማ ከእንግዶቹ መካከል ይገኙበታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!