የሀገር ውስጥ ዜና

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል

By Feven Bishaw

October 03, 2021

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢፌዲሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ጉባኤ ላይም ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን÷ የጉባኤው ሂደትም በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ይሆናል ተብሏል፡፡