የሀገር ውስጥ ዜና

ኢሬቻ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ያደረጋችሁትን ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

By Meseret Awoke

October 03, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የፍቅር ፣ የይቅርታ እና የአንድነት በዓል የሆነውን ኢሬቻን በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ያደረጋችሁትን ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

የ2014 ዓ.ም ኢሬቻ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አክብረናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ኢሬቻ የምስጋና ፣ የዕርቅ እና የሰላም በዓል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የፍቅር ፣ የይቅርታ እና የአንድነት በዓሉን በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ያደረጋችሁትን ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!