Fana: At a Speed of Life!

7ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ አውደ ርዕይ፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ አውደ ርዕይ፣ ባዛርና ሲምፖዚየም በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
 
አውደ ርዕዩ ”የህብረት ስራ ግብይት ለሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
 
የፌደራል የኅብረት ሥራ ኤጄንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲ ሙሃመድ፥ በሀገሪቱ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲፈጠር ሰው ሠራሽ የሆኑ እና በከተሞች የሚከሰቱ የዋጋ ንረቶች እንዲስተካከሉ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
 
አውደ ርዕዩ በህብረት ስራ ማህበራት መካከል ጠንካራና የተፋጠነ የገበያ ትስስርን ለመፍጠርና ማህበራት ለሰላም መስፈንና ለትብብር የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ በተጨባጭ ለማሳየት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑንም አንስተዋል።
 
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ 175 የህብረቱ ማህበራት እና አጋር ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
 
በሀገር አቀፍ ሲምፖዚየሙ ላይ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት የኅብረት ሥራ ልዩ ተሞክሮዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.