Fana: At a Speed of Life!

በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት ማገልገል ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ ውሳኔ ተገዥነትንም ጭምር የሚያመለክት ነው- መከላከያ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት ማገልገል ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ ውሳኔ ተገዥነትንም ጭምር እንደሚያመለክት መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ፥ በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 8 ቁጥር 2 ላይ “… ይህ ሕገ-መንግሥት የሉዓላዊነታቸው መገለጫ ።” እንደሚል ገልጸው፣ “በመሆኑም የመከላከያ ሠራዊት ቃሉን ጠብቆ በከፈለው እልህ አስጨራሽ መሥዋዕትነት ሕዝብ ለመረጠው የመንግሥት ምሥረታ በቅቷል።” ብለዋል።
“በዚህም በጓዶቻችን መሥዋዕትነት ለተመሠረተው መንግሥት መብቃታችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለንን ታማኝነት ያረጋገጥንበት ስለሆነ ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን ከዚህ ስለደረስን ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል” ሲሉ ገልጸዋል።
“ሥልጣን በምርጫ ብቻ የሚያዝ እንጂ በማንኛውም አቋራጭ መንገድ የሚፈፀም አለመሆኑን ሕገ-መንግሥቱ ደንግጓል፤ ሠራዊቱም ለዚህ ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ እውናዊነት ታሪክ የሚያወሳው ዋጋ ከፍሏል” ም ብለዋል።
ኮ/ል ጌትነት፣ “የመከላከያ ሠራዊት ቃሉን ጠብቆ ለሕግ የበላይነት ሲተጋ የመጨረሻ ምሽግ መሆኑን ያወቁ ሀገር አፍራሽ ኃይሎች ከውጭ እና ከውስጥ ያላቸውን አማራጮች ሁሉ ተጠቅመው ገጥመውናል። ይሁን እንጂ ደማችን ጎርፍ ሆኖ ወስዷቸዋል፤ አጥንታችን እሾክ ሆኖ ወግቷቸዋል፤ ያፈረሱት ቃል እንጂ ሀገር እንደሌለ አሳይተናቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
ወደፊትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመረጠው መንግሥት በመታዘዝ እና የኢትዮጵያን አንድነት ዛሬም እንደትናንቱ በትግላችን የታፈረች እና የተከበረች ሀገር ለመጭው ትውልድ እንደምናስረክብ እርግጠኞች ነን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, standing and military uniform
78,985
People Reached
3,630
Engagements
Boost Post
2.2K
37 Comments
101 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.