Fana: At a Speed of Life!

በዱር በገደሉ ላሉት የመከላከያ ሰራዊትና ለጸጥታ አካላት ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በዱር በገደሉ ላሉት የመከላከያ ሰራዊትና ለጸጥታ አካላት ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ ግልጽና ተዓማኒ ምርጫ በማድረግ ህዝባዊ ቅቡል መንግስት ለመመስረት ያበቃንን ፈጣሪ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በዱር በገደሉ ላሉት የመከላከያ ሰራዊትና ለጸጥታ አካላት ያለኝን አክብሮትና ምስጋና እገልጻለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ውለታችሁን አትረሳምም ነው ያሉት፡፡
መርከቢቱ ኢትዮጵያ የእኩልነት እና የነጻነት ሀገር ናት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።
በየትኛውም ዘመን የእናት ሀገር ጥቃት ሲመጣ የግል ቅሬታውን ወደ ጎን አድርጎ በአንድነት ይነሳል ለዚህም ታላቅ አክብሮቴን እገልጻለሁ ብለዋል፡፡
ነብር ዝንጉርጉርነቱን እንደሚባለው ኢትዮ ዮጵያዊ ማንነቱን አይለቅም፡፡
ኢትዮጵያ በአርኪዮሎጂ ዘርፍም ቀደምት ምድር መሆኗ ተረጋግጧል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.