Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻነት እናት ናት – ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለመላው ኢትየጵያ ህዝብ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለምታደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ የኬንያ ህዝብ እና መንግስት ከጎናችሁ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻነት እናት ናት ፣ ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛች ሀገር ናት ብለዋል።

አፍሪካውያን ዛሬ ነጻ ወጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እናት እንደመሆኗ እናት ደግሞ ሰላም ካልሆነች ቤተሰብ ሰላም አይሆንም ብለዋል።

የኢትዮጵያን ሰላም ማረጋገጥ የአፍሪካን ሰላም ማረጋገጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.