የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ

By Feven Bishaw

October 05, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል አስታወቀ፡፡

ግብረ ሀይሉ በመስቀል አደባባይ የተከናወነው ሥነ-ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪዎች ላሳዩት ጨዋነት ለተሞላበት ቀና ትብብርና ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በፍፁም ሙያዊ ብቃት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላትና የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል ምስጋና አቅርቧል።