Fana: At a Speed of Life!

የኤክስፖ 2020 ዱባይ የኢትዮጵያ ፖቪሊዎን ለጉብኝት በይፋ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዱባይ በሚካሄደዉ ኤክስፖ 2020 በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን ደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋና አረጋ እና የኤክስፖ 2020 ዱባይ የኢትዮጵያ ኮሚሽነር ጄኔራል፣ አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማሪያም በዱባይ የኢፌዲሪ ቆንስል ጄኔራል እንዲሁም የንግድና ኢንዱስትሪ ኃላፊዎች በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የተለያዩ አደረጃጀት ኃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
ኤክስፖው በፈረንጆቹ ከጥቅምት 1 ቀን 2021 እስከ መጋቢት 31 ቀን 2022 ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አምባሳደር ምስጋናዉ አረጋ ባደረጉት ንግግር፥ የዱባይ ኤክስፖ 2020 የአገራችንን ባህል፣ ታሪክ፣ የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲሁም የቱሪስት መስህብን ለማስተዋወቅና ገጽታችንን ለመገንባት ትልቅ ድርሻ እንዳለዉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አገር በፖቪሊዎን(Pavillion) እንደምትካፈልና ተሳትፎዋን የተመለከተ ገለጻ አድርገው፥ ለዝግጅቱ መሳካት በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የተለያዪ አደረጃጀት ኃላፊዎች፤ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለሚኖሩ ህፃናትና ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል ።
በኤክሰፖዉ የኢትዮጵያ ምርቶች የሚቀርቡበት፣የቱሪዝም ተደራሽነት የምናሳደግበት እንዲሁም የኢንቨስትመንት እድሎችን የምናስተዋወቅበት ትልቅ መድረክ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች መገኛ የሃይማኖቶች መቻቻል አብሮነት በሚገልጽና ኢትዮጵያ እንደ አገር ምድረ ቀደምት( Land of Origin and Opportunity) በሚሉ መሪ ቃሎች ዳያስፖራዉን ያሳተፉ ልዪ ልዪ ዝግጅቶች በስድስት ወራት ዉስጥ እንደሚቀርቡና እንዲጎበኙ በድጋሚ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከውጭ ጉዳ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+5
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.